የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ISO Certified ለሆኑ የአማራ ክልል ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅዎች እውቅ ሰጠ!!
ለባህርዳር ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅና ለጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በትምህርት ስራ አመራር ስርዓት (ISO 21001) ፣ ድረጅቱ በሥራ አመራር ሥርዓቶች ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን መሟላታቸውን በተከናወነላቸው የኦዲት ሂደት ተገምግሞ መረጋገጫ በመሰጠቱ የእውቅና ሰርትፊኬት ተረክበዋል ።
በሰርተፍኬቱ ርክክብ ወቅት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ በቅድሚያ የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት በማስተላለፍ በዓለም አቀፍ የስራ አመራር ስርዓቶች ሰርተፍኬት ማግኘታቸው ለሚሰጡት አገልግሎት በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲሆኑ አስቻይ መሆኑን አብራርቷል።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እንዲሁም አጠቃላይ ስለ የጥራት መንደር የተቀላቀሉ በመሆናችሁ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
የአብክመ ስራ ክህሎት ቢሮም የሁለቱ ኮሌጅዎች ( ISo 21001) certified የመሆን ስኬት የክልሉ ፣የኮሌጅዎች አመራሮች ሌት ተቀን ያላሳለሰ የስራ ትጋት እና ሌሎች ባለድርሻ ጋር በትብብር በመስራት የተገኘ በመሆኑ በስራ ሂደቱ ተሳትፎ የነበራቸው የኮሌጅዎች አመራሮች ፣የኮሌጅ ስራ አመራር አባላት ፣ባለሙያዎች እና መላው ኮሌጅዎች ቤተሰቦች በሙሉ እንኴን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን